Skip to main content

ኢትዮጵያ:- እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይገባ መከልከል ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖችን የሚጎዳ ነው

ምግብና መድሐኒት በአፋጣኝ እንዲገባ ይፈቀድ፤ ዓለም አቀፍ ማጣራት እንዲካሄድ ደግፉ

  • የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ወደምትገኘው ትግራይ እርዳታ እንዳይገባ መከልከሉ፣ በክልሉ የጤና ተቋማት ከመውደማቸው ጋር ተደምሮ፣ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖች የድሕረ ፆታዊ ጥቃት አገልግሎት እንዳያገኙ አድርጓቸው ይገኛል።
  • መንግስት ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ ትግራይን ሙሉ በሙሉ መዝጋቱም ተጠቂዎች ወሳኝ የሆኑ የሕክምናና የስነ አእምሯዊ ድጋፎች እንዳያገኙ አድርጓቸዋል።
  • የአፍሪካ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ዓለም አቀፍ እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶች የተፈፀሙት በደሎች በዓለም አቀፍ አጣሪ ኣካል እንዲመረመሩ ድጋፋቸውን እንዲሰጡና በጦርነቱ እየተሳተፉ ያሉት ሁሉም ሐይሎች ግፎችን መፈፀም እንዲያቆሙ እንዲሁም እርዳታ ባስቸከይና ያለ ምንም መስተጓጐል እንዲገባ እንዲፈቅዱ ተፅእኖ ሊያሳርፉ ይገባል።  
Read a text description of this video

Sexual violence was used as a weapon of war in Tigray.    

But the abuse didn’t end there.  

Ethiopian forces and allies destroyed and pillaged health centers. 

The Ethiopian government blocked access to medical aid, food and basic services.   

Sexual violence survivors need critical health care and psychosocial support. 

Ethiopia Should Allow aid into Tigray. 

    (ኒውዮርክ) - የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ወደምትገኘው ትግራይ እርዳታ እንዳይገባ መከልከሉ፣ በክልሉ የጤና ተቋማት ከመውደማቸው ጋር ተደምሮ፣ ፆታዊ ጥቃት (ወሲባዊ ጥቃት) የደረሰባቸው ወገኖች የድሕረ ፆታዊ ጥቃት አገልግሎት እንዳያገኙ አድርጓቸዋል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።

    ባለ 89 ገፅና “ያችን ቀን ሁሌም አስታውሳታለሁ:- አገልግሎት በኢትዮጵያ፣ በትግራይ ክልል ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ወገኖች” በሚል አርእስት የወጣው ሪፖርት በትግራይ ሕዳር ወር 2013 ዓ.ም. ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ከ6 እስከ 80 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖች ያጋጠማቸውን የጤና ጉዳት፣ ጠባሳና መገለል ሰንዷል። ሂዩማን ራይትስ ዎች የትግራይ መንግስት ትግራይን ሙሉ በሙሉ መዝጋቱ ያስከፈለው ሰብኣዊ ዋጋ ላይ አፅንኦት ሰጥቷል። በዚህ ምክንያት የተጠቂዎች ፍላጎት በቂ እና ዘላቂ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዳያገኝና የወደመው የክልሉ የጤና ስርዓት ዳግም እንዳይቋቋም ምኽንያት ሆኗልና።

    በትግራዩ ጦርነት የመጀመርያዎቹ ዘጠኝ ወራት ተፋላሚ ሐይሎች መጠነ ሰፊ ፆታዊ ጥቃቶችን የፈፀሙ ሲሆን ሆን ብለው የጤና ተቋማትን የጥቃታቸው ዒላማ አድርገዋል፤ ይህም ተጠቂዎቹንና መላውን ህበረተሰብ ለከፍተኛ ችግሮች ዳርጓል ይላሉ በሂዩማን ራይትስ ዎች የሴቶች መብት ዳይሬክተር ኒሻ ቫርያ። “መንግስት ካለፈው ሰኔ ጀምሮ ትግራይን ሙሉ  በሙሉ መዝጋቱም ተጠቂዎች ሕክምናዊና ስነ አእምሯዊ ድጋፎችን እንዳያገኙ አድርጓል።”

    የአፍሪካ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ዓለም አቀፍ እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሐትን ጨምሮ በጦርነቱ እየተሳተፉ ያሉት ሁሉም ሐይሎች ግፎችን መፈፀም እንዲያቆሙና እርዳታ ባስቸከይና ያለ ምንም መስተጓጐል እንዲገባ እንዲፈቅዱ ተፅእኖ ሊያሳርፉ፣ የተፈፀሙት በደሎችም በገለልተኛ ዓለም አቀፍ አጣሪ ኣካል እንዲመረመሩ ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል።

    ሂዩማን ራይትስ ዎች 28 የጤና እና የእርዳታ ሰራተኞች፣ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖችና የዓይን ምስክሮችን ጠይቋል። በተጨማሪም ሂዩማን ራይትስ ዎች የግለሰቦች ማንነት በማይገልፅ መንገድ ከአገልግሎት ሰጪ አካላት ያገኛቸው ሌሎች 43 ሕክምናዊ  የተጠቂዎች ሰነዶችን የመረመረ ሲሆን ከትግራይ ባለስልጣናት በስልክና በፅሑፍ ቃለ መጠይቅ ኣካሂዷል። ሂዩማን ራይትስ ዎች የጥናቱ ውጤት ዋና ጭብጥና የመረጃ ጥያቄ ለፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት የላከ ቢሆንም ምላሽ ግን አላገኘም።

    በትግራይ እየተካሄደ ባለው ጦርነት በኢትዮጵያና በኤርትራ ሰራዊት እንዲሁም በኣማራ ክልል ሚልሻዎች መጠነ ሰፊ ፆታዊ ጥቃቶች መፈፀማቸው የሚያሳዩ ሪፖርቶች አሉ። እነዚህ ጥቃቶች አስገድዶ መድፈር፣ በጅምላ አስገድዶ መድፈር፣ ፆታዊ ባርነትና ማሰቃየትን ያጠቃለሉ ሲሆኑ አብዛኛው ግዜ ደግሞ በቤተሰብ አባላት ላይ በሚፈፀሙ ግድያዎች፣ ግርፊያና ጎሳ-ተኮር ስድቦችና ማዋረድ የታጀቡ ናቸው። የትግራይ ተፋላሚ ሐይሎችም በክልሉ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ፆታዊ ጥቃት፣ ግድያና ሌሎች ግፎችን በመፈፀም፣ በአማራ ክልል ደግሞ በሲቪል አማራዎች ላይ ተመሳሳይ በደል ፈፅመዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

    ሂዩማን ራይትስ ዎች ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖች ከሚፈልጉት የጤና አገልግሎቶች መካከል፣ ፅንስን ማቋረጥ፣ የኤች ኣይ ቪ ኤድስ ሕክምና፣ ሂፒታይቲስ ቢ እና የአጥንት ስብራት ሕክምና፣ በቢላ መወጋት፣ ስር የሰደደ ጠባሳና ፊስቱላ ይገኙባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠቂዎች የጭንቀትና የስነ አእምሮ ጠባሳ ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው ታይቷል።

    A service provider supports a survivor of sexual violence in Tigray region, Ethiopia, February 27, 2021. © 2021 Eduardo Soteras/AFP via Getty Images

    “አንድ ቀን፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች አንዲት ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ልጃገረድ ወደ ሆስፒታሉ ይዘዋት መጡ” ይላል በአንድ የከተማ ሆስፒታል እሚሰራ ዶክተር።  “መረመርናት እና እርጉዝ መሆኗን አረጋገጥን። መቀሌ አጠገብ በሚገኝ የገረብ ግባ ወታደራዊ ካምፕ በፆታዊ ባርነት ስር ከነበሩት አንዷ ናት።” ሂፒታይቲስ በሽታ እንደነበራት ዶክተሩ ይናገራል።  “በራሷ ፈቃድ ፅንሱን አስወረድንላት። የሂፔታይቲስ መድሀኒትም ሰጠናት። ከዛ በኋላ ብዙ ሴቶችና ልጃገረዶች መመድሀኒት ለማግኘትና ፅንስ ለማቋረጥ ይመጡ ነበር። አብዛኞቹ በጦርነቱ በሚሳተፉ ሐይሎች በተለይም በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች የተደፈሩ ነበሩ።

    በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ 9 ወራት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የአማራ ሐይሎች በትግራይ የጤና ተቋማትን ዘርፈዋል፣ አውድመዋል። ይህ ሁኔታ በየመንገዱ ባሉት የፍተሻ ጣብያዎች፣ በጤና ተቋማቱ ውስጥ ወይም በአጠገቡ ወታደሮች ከመኖራቸው ጋር ተሳስሮ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖች በተለይም ከከተማ ውጪ ያሉት በነዛ እርግዝናን እና ኤች ኣይ ቪ ኤድስን ለመከላከል ዕድል የሚሰጡ ወሳኞቹ የመጀመሪያ 72 ሰዓታት ሕክምና እንዳያገኙ አድርጓቸዋል። አንድ ሰብኣዊ እርዳታ ሰጪ እንዳለው በድርጅታቸው አገልግሎት ለማግኘት ከሚመጡ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖች ከ80 በመቶ በላይ በመጀመሪያዎቹ 72 ሰዓታት አልደረሱም።

    የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሰኔ ወር መገባደጃ የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጁ በኋላ መንግስት ክልሉን ከበባ ውስጥ አስገብቶታል። ክልከላው ምግብ፣ መድሀኒት፣ ገንዘብና ነዳጅ ያጠቃለለ ሲሆን ዓለም አቀፍ የሰብኣውነት ህግን የሚፃረር ነው። ይህም የጤና አገልግሎቶች እንዳያንሰራሩ ዕንቅፋት ሆኗል።

    እርዳታ ሰጪ ድርጀቶች ዓለም አቀፍ ደረጃን ያሟላ ምላሽ መስጠትና ማጠናከር እንዳልቻሉ ሂዩማን ራይትስ ዎች ይገልፃል። ማንኛውም የተጠናከረ ምላሽ ያሉትን ዓበይት ክፍተቶች የሚሞላ ሊሆን ይገባል። ይህ ደግሞ በሕብረተሰብ ደረጃ  ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል ስርዓትን የመኖር አስፈላጊነት፣ ለሴቶችና ለልጃገረዶች ዋስትና ያለው አከባቢን መፍጠር፣ ምቹ የፆታዊ ጥቃት ሕክምናዊ አስተዳደር፣ የስነ አእምሮ ጤና አገልግሎት፣ የስነ አእምሮና ማሕበራዊ አገልገሎት ድጋፎችና ልዩ እንክብካቤዎችን ያጠቃለለ ነው። እነዚህ ሁሉ አገልግሎቶች ለሁሉም ተደራሽና ልዩ ሁኔታ ያለባቸውና የአካል ጉዳተኞች፣ እንዲሁም የሽማግሌዎችና የህፃናት ፍላጎቶችን ከግምት ያስገቡ ሊሆኑ ይገባል። በትንሽ ድጋፍና ግዙፍ ተግዳሮቶች አስጨናቂ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት ባለሙያዎችም ጭምር የስነ አእምሮ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል።

    ትግራይ ውስጥ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የደረሰው ፆታዊ ጥቃት፣ በፌዴራላዊ መንግስቱ ተግባራት ምክንያት በተጠቂዎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ግፎች፣ እንዲሁም የትግራይ ሀይሎች በአማራ ክልል በሲቪል አማሮች የሚፈፅሙት ጥቃት የሚያመለክተው ነገር ቢኖር፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሰብኣዊ እርዳታ ማደናቀፍን ጨምሮ ከግጭቱ ጋር የተዛመዱ ግፎችን ለማጣራት ነፃ መመርማሪ ኣካል ሊቋቋም እንደሚገባ ነው ይላል ሂዩማን ራይትስ ዎች።

    “አውዳሚው ጦርነት ትግራይ ውስጥ ከተነሳ ከአንድ ዓመት ወዲህ፣ አስገድዶ መድፈር፣ በጅምላ አስገድዶ መድፈርና ፆታዊ ባርነት ለደረሰባቸው ወገኖች የአንገብጋቢና የረዥም ግዜ አገልግሎት፣ እንክብካቤና ድጋፍ በኣብዛኛው የሉም” ይላሉ ቫርያ። የትግራይ ሴቶችና ልጃገረዶች ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ግፎች ደርሶባቸዋል ብቻ ሳይሆን እንዲድኑና ህይወታቸውን ዳግም እንዲገነቡ ወሳኝ ሚና ያላቸው ምግብ፣ መድሀኒቶች፣ ልዩ እንክብካቤና ሕብረተሰብን መሰረት ያደረገ ድጋፍ በማግኘት ረገድ እጅግ ኣስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

    Your tax deductible gift can help stop human rights violations and save lives around the world.

    Region / Country